Your cart is currently empty!
ገዳ ባንክ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 19, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የሐራጅ ማስታወቂያ
ገዳ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/1992 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
የጨረታው ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የወጣው |
||||||
|
ከተማ |
ቀበሌ/ወረዳ |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ቁጥር |
የቦታ ስፋት በካ.ሜ |
ቀን |
ሰዓት |
||||||||
|
አቶ አድማሱ በቀለ መኩሪያ |
አቶ አድማሱ በቀለ መኩሪያ |
የንግድ ቤት |
አባ መላ |
ሻሻማኔ |
ቢሻን ጉራቻ |
WLM/0527/15 |
10‚000 |
11‚853‚304.13 |
09/03/2018 |
4:00-6:00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
||
|
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የተሸከርካሪው አይነት፣ የሚገኝበት አድራሻ፣ የሰሌዳ ቁጥርና ሞተር ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታው ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የወጣው |
||||||||
|
የመኪና አይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሰራበት ዘመን |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
ቀን |
ሰዓት |
||||||
|
አቶ ቶማስ ጥላሁን ሰቦቃ |
አቶ ቶማስ ጥላሁን ሰቦቃ |
ቻይና ቢዋይዲ የቤት አውቶሞቢል |
አዲስ አበባ ጎተራ ወንጌላዊት ህንፃ ፊት ለፊት የሚገኝ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት |
02-አአ-C58982 |
2024
|
LC0C76C46R4187847 |
BYD472QA*824071003* |
3‚900‚000.00
|
24/02/2018
|
4:00-6፡00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
||
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ጎተራ ወንጌላዊት ህንፃ አከባቢ በሚገኝ ገዳ ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ላይ ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ ባለ ዕዳዎች እና ታዛቢዎች ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- ድርጅቶች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተረጋግጦ የተመዘገበ የመመስረቻ ፅሁፍ እና እንደአስፈላጊነቱ መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለ-ጉባኤዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡
- በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀውን ክፍያ ይከፍላል፡፡
- የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ የሚከፈለውን ክፍያ ለመክፈል ንብረቱ በሚገኝበት ወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር በመቅረብ የሊዝ ውል መዋዋል አለበት፡፡
- ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዘው ለመጎብኘት ይቻላሉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0920885734 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡