Your cart is currently empty!
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ህብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፣ በር፣ መስኮት፣ የመብራት መስመር ዝርጋታ፣ የግድግዳ ሶኬት እድሳት ጥገና፣ የቧንቧ መስመር እና የሽንት ቤት መስመር ጥገና እና እድሳት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ህብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የጥገና እና እድሳት አወዳድረን ማሰራት ስለምንፈልግ
በዚህም መሰረት፡-
- ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና
- ሎት 2. በር፣ መስኮት፣ የመብራት መስመር ዝርጋታ፣የግድግዳ ሶኬት እድሳት ጥገና “
- ሎት 3. የቧንቧ መስመር እና የሽንት ቤት መስመር ጥገና
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው በመስኩ ህጋዊ ሰነድ እና ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሆኑና ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ሙሉ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና አድራሻ መፃፍ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል በአራዳ ክ/ከተማ ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛ ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ በሎት 2 የተጠቀሱ የጥገና ስራዎችን በጠቅላላ የድምር ዋጋ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ይሆናል ተቋም ውል የሚገባው።
- ተጫራቾች ሁሉም የጥገና ስራዎች በአካል መታችሁ ተቁዋሙ በሚያሳያቸው መሰረት አይታችሁ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ ከተቋሙ ጋር ውል ለመዋዋል በቅድሚያ የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዘርፎች ከራሳቸው እቃ ገዝተወ ጥገና የሚያከናውኑ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- ፒያሳ ከመብራት ኃይል ወደ እሪበከንቱ በሚወስደው መንገድ ጎጀብ ጥርስ ህከምና ጎን
ለበለጠ ማብራሪያና ጥያቄ
ስልክ ቁጥር፦ 09-12-85-03-39/ 09-11-38-31-11
በአራዳ ክ/ከተማ ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Finishig Works cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Furniture cttx, cttx House Furniture cttx, cttx Installation, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Others cttx, cttx Sewerage cttx, cttx Water Construction cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx, cttx Water System Installation cttx, cttx Wood and Wood Working cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Maintenance and Other Engineering Services cttx