በደቡብ ኢትዮጵያ መንግሥት በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል የፋብሪካ ውጤቶች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ የሞተር ሣይክል፣ የመኪና ጥገና እና የመለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ መንግሥት በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት

  • በሎት 1. የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣
  • በሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • በሎት 3. ለግንባታ አገልግሎት የሚውል የፋብሪካ ውጤቶች፣
  • በሎት 4. የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤
  • በሎት 5. የሞተር ሣይክል፣
  • በሎት 6. የመኪና ጥገና እና የመለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ጨረታው የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉትን ይጋብዛል።

1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንገድ ሥራ ፈቃድ፣

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፣

5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/ትችል፣

6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አሥራ አምስት/ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል የጨረታው ሰነድ እስከ 11፡30 ሰዓት ከገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ኬዚ ቲም ቢሮ ቁጥር-13 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 3000 /ሦስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ “CPO” ማስያዝ አስባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በገዙት ሰነድ መሠረት በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በታሸገው ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ማለትም ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓላት ቀናት ሳይጨምር/ በዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በ16ኛው የሥራ ቀን 6፡30 ድረስ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁ.13 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት ወዲያውኑ ታሽጎ በዚያውኑ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጉ ዕቃዎች መ ቤቱ ባስቀመጠው ቀን ማቅረብ ግዴታ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን፣ ይህም ሲባል ጨረታው በመሠረዙ ተጫራቾች

በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-242 0191/09 66 89-55 30/ 09 13 21 56 94 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት