የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር እና የድልድይ ቤሪንግ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 08/2018

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር እና የድልድይ ቤሪንግ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዛው ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ጋቢዮን እና የድልድይ ቤሪንግ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197969 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 11/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 26/02/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ 1 ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦሪጅናል ከፋይናንሺል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፤ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500.000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ11/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 26/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታክስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማውረጃ ወጭን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መመያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን 26/02/2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 ሰዓት ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ወይም በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  12. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋከስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-5155/ 058-222-1107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ

ፖ.ሣ.ቁ 382

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *