Your cart is currently empty!
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የእቃ ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ገላን 2ኛ/ደ/ት/ቤት/001/2018
በአኢቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የእቃ ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- Lot 1. የቋሚ እቃዎች
- Lot 2. የጽዳት እቃዎች
- Lot 3 የደንብ ልብስ
- Lot 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች
- Lot 5 የስፖርት ዕቃዎች
- Lot 6. አላቂ የትምህርት እቃዎች
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN number) ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
4.ተጫራቾች በአቅራቢዎችዝርዝርየተመዘገቡመሆናቸውንየሚገልጽመረጃማቅረብአለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
- Lot 1. የቋሚ እቃዎች ብር…24,000.00
- Lot 2 የጽዳት እቃዎች ብር…..27,000.00
- Lot 3 የደንብ ልብስ ብር….18,000.00
- Lot 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር…..34,000.00
- Lot 5. የስፖርት ዕቃዎች ብር…6,000.00
- Lot 6. አላቂ የትምህርት እቃዎች ብር…8,000.00
በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በተቀመጠው መሰረት ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የሚያሲዙት CPO ህጋዊ ከሆነ ባንክ የተሰራ መሆን አለበት።
7. ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች የሃገር ውስጥ ምርትላይ ተሳታፊ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከሚመለከታቸው ህጋዊ አካል ካላመጡ የሰነድ ማስከበሪያ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ሎት ማሲያዝ አለባቸው።
8. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 5 ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
9. ማንኛውም ተጫራቾች ተወዳድረው አሸናፊ መሆናቸውን ከአረጋገጡ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማቅረብ አለባቸው።
10. ተወዳዳሪዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲያቀርቡና የሚያቀርቡትን የእቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
12. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ቢሮ ቁጥር 5 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
13. ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማህተም በማድረግና አስፈላጊ ሰነዶችን በሟሟላት በሁለት ኮፒ እና ኦርጂናል ኤንቨሎፕ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
15.ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ ለገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማስረከብ አለባቸው።
16. ተጫራቾች የሚሞሉት የአንድ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ገላን ኮንዶሚኒየም
- ተክለሃይማኖት ግሮሰሪ አጠገብ ተጫራቾች ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ካላችሁ በስልክ ቁጥር 011-4-526729 መጠየቅ ይችላሉ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት