Your cart is currently empty!
በኮንሶ ዞን የካራት ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በካራት ዙሪያ ወረዳ ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አላቂ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የፋብሪካ ውጤቶች ግዥ ለመፈፀም በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮንሶ ዞን የካራት ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በካራት ዙሪያ ወረዳ ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አላቂ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የፋብሪካ ውጤቶች ግዥ ለመፈፀም በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
3. በዘርፉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN Number /ያላቸው፣
4. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
5. በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
6. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘውትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በኮንሶ ዞን ካ/ዙ/ወ/ ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት ገቢ አሰባሰብ ዋና የሥራ ሂደት ከፍለው ደረሰኝ በመያዝ በኮንሶ ዞን ካ/ዙ/ወ/ ፋ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. የጨረታ ማስከበሪያ ተጫራቾች 15,000 /አስር አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ/CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦሪጂናል ቴክኒካል ዶክሜንት ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን (የጨረታ ሰነድ) ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናል እንዲሁም ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ አራት በተለያየ ፖስታዎች አሽገው በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሁሉም ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ አድራሻ፣ ስምና ፊርማ በማሳረፍ በ16ተኛው የስራ ቀን ካ/ዙ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. የጨረታው ሳጥን የሚታሽገው በ16ተኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ጨረታው የሚከፈትበት 16ተኛው ቀን የመንግስት መደበኛ የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደትን አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾ የሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተገቢውን ሁሉ መፈፀም ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊነቱ ከተለየ በኋላ እራሱን ከጨረታ የሚያገል ድርጅት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ አግባብ ባለው ህግ ይጠየቃል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-09-14-35-20-77/ 09-45-60-36-00 ላይ ደውስው።
የካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት