Your cart is currently empty!
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር/ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ የደን ውጤቶች ሽያጭ በግልጽ ጨረታ ገዥዎችን አወዳድሮ ሽያጭ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር/ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ የደን ውጤቶች ሽያጭ በግልጽ ጨረታ ገዥዎችን አወዳድሮ ሽያጭ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
1. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን በነጻ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
2. የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
5. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል።
6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ ጽ/ቤት