Your cart is currently empty!
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋ ዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የአይ.ሲ.ቲ.፣ የአይ.ኦ.ኤም.ድ፣ የቢ.ኢ.አይ.፣ የጋርመንት፣ የሆቴል፣ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዕቃዎች እና የተለያዩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ከህሎት ቢሮ የይርጋ ዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሥልጠና እና ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ለ2018 በጀት ዓመት
- አላቂ የጽ/መሣሪያዎች፣
- የአይ.ሲ.ቲ.፣ የአይ.ኦ.ኤም.ድ፣ የቢ.ኢ.አይ.፣ የጋርመንት፣ የሆቴል፣ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዕቃዎች እና
- የተለያዩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የ2018 ዓ.ም የግብር ግዴታውን የተወጣ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉበት የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝና የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት በይርጋ ዓለም ቴከኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፁት የሎት ዓይነቶች በአንዱ ወይም በሁሉም መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልፅ በመሙላት በማኅተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል:: የሚሞላው ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሠነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 20,000/ሃያ ሺህ/ ብር በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማዘጋጀት ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 30% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት
- ጨረታውን አሸንፎ በወቅቱ ውል የማይዋዋል ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ መጓጓዣ እስከ ኮሌጁ የሚያቀርብ ሲሆን ማንኛውም ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በታወጀ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያውኑ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በመከፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የማይገኙ ከሆነ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ወይም 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-225-15-62 መጠየቅ ይችላሉ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋ ዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Foam Mattress cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx Hospitality, cttx Hotel Service Provision cttx, cttx Industrial Machinery Provision and Installation cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Machinery and Equipment cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Networking Equipment and Installation cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Metals cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Products and Services cttx, cttx Raw Materials and Supplies cttx, cttx Stationery cttx, cttx Steel, cttx Steel Raw Materials and Products cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx, Metals and Aluminium cttx, Tour and Travel cttx