በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የቋሚ እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፤ የደንብ ልብስ፤ የትራንስፖርት የአገልግሎት እና የቄብ ዶሮ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 26, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/2018

በቂርቆስ //አስ/በዋና ሥራ አስፈፃሚ /ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዋና ሥራ  አስፈፃሚ /ቤት 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የቋሚ እቃዎች አላቂ እቃዎች፤ የደንብ ልብስ ግዥዎች፤ የትራንስፖርት የአገልግሎት ግዥዎች እና የቄብ ዶሮ ግዥ ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ
  • ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ
  • ሎት 3. ዳት እቃዎች ግዥ
  • ሎት 4. የኤሌትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 5. የደንብ ልብስ ግዥ
  • ሎት 6. የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
  • ሎት 7. የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
  • ሎት 8. የቄብ ዶሮ ግዥ

በመሆኑም ተጫራቾች

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ የሥራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር / tin no/የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው።
  2. ተጫራቾች ከግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
  3. ለሚወዳደሩባቸው የአገልግሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፣ ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
  5. የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቄርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲስ ህንፃ 3 ፎቅ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 430 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደ ማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ //አስ/ አዲሱ ህንፃ 9 ፎቅ

ስልክ ቁጥር 0115548264 /08-69-43-66

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ /ቤት