Your cart is currently empty!
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርከሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈለጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ጨረታ ቁጥር 001/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርከሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈለጋል።
በዚሁ መሰረት፡–
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 001/2018 በ22/02/2018 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለጨረታ የቀረበውን ተሽከርካሪዎችን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች።
- ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዲጅታል ብሔራዊ መታወቂያ ያለው።
- ለጨረታ የቀረበው ተሽከርካሪ ሲሆን የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ግቢ በሚገኘው ተሽከርካ መጋዘን ውስጥ ነው።
- የተሽከረካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም።
- በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ 12፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት እና ሪሲት በመውሰድ ተሽከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል።
- ተሸከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲእነኖ የሚገኘው ግቢ ውስጥ ነው።
- ተጫራቾች በተሽከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ለመግዛት ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 5% በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል።
- የሐራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 11 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሸከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ በባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ይቀርባል።
- የጉምሩክ ኮሚሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70/ 09 12 88 57 46 መደወል ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት