Your cart is currently empty!
የተለያዩ ወፍጮዎችን፣ አነስተኛ ጀነሬተር የወፍጮ መለዋወጫ ዕቃዎች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አደም አብራር መሀመድ እና በፍ/ባለዕዳ ዲዋ አይሲት ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/08065 በመጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/11853 በሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ/ም በሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊት ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፍርድ ያረፈባቸው የተለያዩ ወፍጮዎችን አነስተኛ ጀነሬተር የወፍጮ መለዋወጫ ዕቃዎች በባለሙያ ግምት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር በባለሙያ ግምት 2,105,124 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሀያ አራት ብር) ሆኖ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ/ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የሚያዘው 1/4ኛ ብር 526,281 (አምስት መቶ ሀያ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ አንድ ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የተራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት