የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 28, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/18

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ 200 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው /ቤት 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 ከአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ አዲስ አበባ ዋና ግቢ እና ደብረዘይት ስልጠና ማዕከል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚገዙትን ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በኢንስቲትዩቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውል እና 16ኛው ቀን 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

8. ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

9. ኢንስቲትዩቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኢንስቲትዩቱ ገቢ ይደረጋል፡፡

11. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03

ስልክ ቁጥር 0116-454 147 / 0116-453 598 / 0118-694 931

ከሳሊህተ ምህረት ማርያም /ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

አዲስ አበባ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *