Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 02/2018
የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገለ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| NO. | plate No | Brand Type or Model of Vehicles | Chassis Number | Engine No. 
 | Manufacturing Year | Seat сарасity/ 
 | Cubic Capacity cc | 
| 1 | 3-03687AA | Nissan Station Wagon | WRG40200089 | TD42-103368 
 | 1994 
 | 7 
 | 4169 
 | 
| 2 | 3-52352 AA | Nissan Pick up | JNICJUD2ZZ0095766 | OD32271181 
 | 2008 | 5 | 3153 | 
| 3 | 3-52354 AA | Nissan Pick up | JNICJUD2ZZ0095856 | QD32271499 | 2008 | 5 | 3153 | 
| 4 | 3-61394AA | Nissan Pick up | ADNJ980000E006170 | QD32277413 | 2009 | 5 | 3153 | 
| 5 | 3-61395AA | Nissan Pick up | ADNJ980000E006164 | QD32277331 | 2009 | 5 | 3153 | 
| 6 | 3-10460ET | TOYOTA Pick up | YN850055605 | 2Y-0788336 | 1993 | 5 | 1812 | 
| 7 | 3-51714ET | Bishoftu Pick up | EBPH4C4B473001112 | 40402839Z 
 | 2014 | 5 | 2446 | 
| 8 | 3-33073ET | MITSUBISHI Carry | MMBJNK7706F029605 | 4M40NA0630 | 2006 | 5 | 2835 | 
| 9 | 3-42328AA | Nissan Minbus | JNITG4E2520770063 | ZD30132776K | 2007 | 10 | 2953 | 
| 10 | 3-51715ET | Bishoftu Mide bus | EBDHM324051000078 | 2014D000403 | 2014 | 30 | 8226 | 
| 11 | 3-10473ET | TOYOTA Automobile | KE706206295 | 4K-6572619 | 1986 | 5 | 1290 | 
| 12 | 3-12682ET | TOYOTA Pick up | YN85-0055599 | 2Y-078824 | 1993 | 4 | 
 | 
- ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ። በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሠነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት 22 ማዞሪያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የቋሚ ንብረት አስተዳደርና ግቢ ውበት ቡድን ቢሮ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ከጥቅምት 29 ቀን 2018 እስከ ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ድርጅታችን የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዘዋወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የሚገዙት ተሽከርካሪ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺሀ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት፣ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
- የጨረታ ሣጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ህዳር 03 በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የሠራተኞች መዝናኛ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
- ድርጅቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስመ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃሎ በመክፈል ተሽከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለበት።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡_ 0912 03 33 91 ደውስው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ስራ ድርጅት