Your cart is currently empty!
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ አልባሳት፣ ጫማ፣ የቤት ዕቃ፣ እስፔርፓርት፣ ምግብ ነክ፣ ኮንስትራክሽን፣ የፅዳት ዕቃ እና ልዩ ልዩ በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 30, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የግልጽ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣
- የቤት ማስዋቢያ፣
- አልባሳት፣ ጫማ፣
- የቤት ዕቃ፣
- እስፔርፓርት፣
- ምግብ ነክ፣
- ኮንስትራክሽን፣
- የፅዳት ዕቃ እና ልዩ በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች ከ25/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለጹትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡–
- በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
- በሐራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃዎቹን መግዛት 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ፤
- ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ እቃዎቹን ለመግዛት የሚቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
- በግልጽ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ክፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
- እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፤
- በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
- ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
- ተጫራቹ እቃዎችን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ላይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፣
- ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከ25/02/2018 ዓ.ም በ2፡00 ሰዓት ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ27/02/2018 ዓ.ም በ3:45 ሰዓተ ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው በ27/02/2018 ዓ.ም በ4:15 ሰዓት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
N.B: አሽናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕሉን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም::
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Home Appliance and Supplies cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Sales, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Textile, Disposals and Foreclosure cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx