በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶች ለመፈጸም በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ 2018 በጀት ዓመት የትራክተር ኪራይ የመኪና ጎማ ግዥ፣ የቢሮዉ ጥገና፣ ኤሌክትሮኒክስና ሶላር ግዥ፤ የውሃ ቦቲ ኪራይ፣ የመኪና ጥገና ጋራዥ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የህትመትና ማስታወቂያ ሥራዎች፣ የግብርና ኬሚካሎች ግዥ፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳትና ውበት፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች ግዥ የችግኝ እና የተለያዩ የግብርና ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል።

1. ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች

ማለትም፡

1.1 በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ

1.2 የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያለው

1.3 ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው

1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

15 ..

1.6 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ እና

1.7 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ሰዓት በአፋር ብሄራዊ // የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የሕጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና /Big Bond/ ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲ..(C.PO) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፈ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት የውል ማስከበርያ ይመለስላቸዋል።

5. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ /ቤቱ አይቀበልም።

6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው የሥራ ቀን 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በዕለቱ 430 ሰዓት በአፋር ብሄራዊ // የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልክ ቁጥር 033-366-6022 ወይም 033-366-3376 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ

ሠመራ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *