የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 31, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ /የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን ፕሮጀክት እና የመያዣ ንብረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

.

ተበዳሪው የመያዣ ሰጪው/ስም

የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ

የጨረታው መነሻ ዋጋ

ደረጃ

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት

1

ኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ /የተ/የግ/ማህበር

በኦሮሚያ //መንግሥት በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ አዋሽ ብሾላ ቀበሌ ውስጥ 1 ሄክታር ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ የእንስሳት ማረጃ ማሽኖች፣ ጀኔሬተር እና አንድ ባለ ማቀዝቀዣ ዩዲ ኒሳን ተሽከርካሪ

44,999,333.61

1

በኢትዮጵያ ልማት ባን አዳማ ዲስትሪክት /ቤት ኅዳር 26 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት

ማሳሰቢያ፡

1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት የሚገዙበትን ዋጋ ስምና አድራሻ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት /ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 26 ቀን 2018 . 330 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መውሰድ ይችላሉ።

4. ንብረቱን በብድር መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የባንኩን የብድር መስፈርት ማሟላትና ንብረቱን የሚገዙበት ዋጋ፣ ስለ ቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ሁኔታ፣ ለቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ከሚገዙት ንብረት በተጨማሪ የሚያቀርቡት የመያዣ አይነት፣ ግምትና የሚገኝበት ቦታ በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርበታል።

5. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን .. ተመላሽ ይደረጋል።

6. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግሥት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል ይገደዳል።

7. የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።

8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መሥሪያ ቤት ናፍራን ሕንፃ 3 ፎቅ በአካል በመቅረብ ማነጋገር እና ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-022-212-04-17 ላይ መደወል ይቻላል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት