Your cart is currently empty!
ኦሮሚያ ባንክ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Jan 25, 2026)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ |
ጨረታው የወጣው |
||
|
ከተማ፣ ክ/ከ/ወረዳ/ ቀበሌ |
የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር |
የቦታ ስፋት በካ.ሜ/ሄክ |
||||||||
|
1 |
አቶ ካህሳይ ካሳሁን ገ/እየሱስ |
ጂ.ኤፍ ላይፍ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር |
የአግሮ–ኢንዱስትሪ ህንጻ እና የወተትና የወተት ተዋዕፆ ማቀነባበሪያ ማሽን |
አፍሪካ ጎዳና |
ኦሮሚያ ክልል፣ ሱሉልታ ከተማ፣ቀበሌ 01 |
SUL/731/10 |
2000 |
14,146,024.74 |
የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ዋና መስሪያ ቤት |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል:: በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል::
2. ተራ ቁጥር 1 ንብረቶች ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አካባቢ አምራን ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ ምክትል ቺፍ ኦፊሰር ህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል:: ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል::
3. የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል:: የጨረታ መጠናቀቂያ ስዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል:: በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል::
4. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል:: በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል::
5. በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል::
6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል:: ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል::
7. ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል::
8. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ::
9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 እና ወይም 251 91 97 49 020 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት፣ ለተራ ቁ.1 በ 0115-58-52-78 / 58-63-87 ኦሮሚያ ባንክ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል::
10. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኦሮሚያ ባንክ