Your cart is currently empty!
የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ስፋቱ 500 ካ.ሜ በሆነ የመሬት ይዞታ ላይ የሚገኝ የቦታው ደረጃ ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ቦታ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Jan 27, 2026)
በአፈጻጸም ከሳሾች
- አቶ በለጠ ጣሰው
- ወ/ሮ ስመኝ አስፋውና
በአፈጻጸም ተከሳሽ የአቶ ግዛው መግራ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ክርክር ጉዳይ አስመለክቶ የአፈጻጸም ተከሳሽ የአቶ ግዛው መግራ ንብረት የሆነው የካርታ ቁጥር ዲ/ኪው/08/3 የሆነው ቤት በ8/6/2013 ዓ.ም ተሰጥቶ ያለው ስፋቱ 500 ካ.ሜ በሆነ የመሬት ይዞታ ላይ የሚገኘው የሚገኝበት ቦታ በቢሾፍቱ ከተማ በቀድሞ ስሙ ዲ/ኪው ቀበሌ በአሁኑ አገላለጽ ደካ ቦራ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቦታው ደረጃ ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል መሆኑን እና የመነሻው ዋጋ ብር 1,190,307 35 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ሺህ ሶስት መቶ ሰባት ብር ከ35/100) የሆነው እና መግዛት የሚፈልግ ሰው አስቀድሞ ብር 297,577 (ሁለት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሰባት ብር) በሲፒኦ በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ስም በየትኛውም ባንክ በማስያስ በጨረታው ላይ በ 21/6/2018 ዓ.ም ቤቱ በሚገኝበት ስፍራ በመገኘት ከ3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ እና ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 እስከ 11፡00 ጨረታው የሚካሄድ መሆኑን በመግለጽ ለ30 ቀን አየር ላይ እንድታውሉት እያሳወቅን 1 (አንድ) ገጽ የላክንላችሁ ስለሆነ እንድታትሙት እና ውጤቱን ለቀነ ቀጠሮ 24/6/2018 ዓ.ም በ10፡00 ላይ ሪፖርት እንድታደርጉ የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አዟል።
የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት