Your cart is currently empty!
በአራዳ ከፍለ ከተማ የወረዳ 4 ፋይናንስ ፅ/ቤት የፅዳት እቃዎች፣ የእስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ መስተንግዶ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የድንኳን ስራዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ህትመት ስራ እና የኮምፒውተር ጥገና አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 03, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ከፍለ ከተማ የወረዳ 4 ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018ዓ/ም በጀት ዓመት በጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም የ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት-1 የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት-2 የእስቴሽነሪ ዕቃዎች፣
- ሎት3 የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣
- ሎት4 መስተንግዶ፣
- ሎት5 የትራንስፖርት አገልግሎት፣
- ሎት 6 የድንኳን ስራዎች፣
- ሎት7 የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት8 ህትመት ስራ፤
- ሎት9 የኮምፒውተር ጥገና አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በሙያው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በተሰማሩበት የስራ መስከ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ እና የከሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ሊስት ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- ከዚህ በፊት በጨረታ ስራዎች ላይ ያላቸውን የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የስራ አፈፃፀም ደብዳቤ ቢኖር ይመረጣል፤
- የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር በመከፈል መጫረት ይችላሉ፤
- የጨረታ ሰነዶቻችሁን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በመሙላት ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለተጫረቱበት ሎት ላይ 2% በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእዛው እለት በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ /ከተማ በወረዳ 4 አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ከገዙበት ጨረታ ሰነድ የዋጋ መሙያ ፎርም ውጭ ዋጋ ተሞልቶ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ሌላው ናሙና እስከ (10) አስረኛው ቀን ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 % በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ(CPO) ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጊዜና የዋጋ ገደብ ማስቀመጥ አይቻልም።
አድራሻ:- የአራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ልዩ ቦታ ሾላ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወደ ቀጨኔ የሚወስደው መንገድ 50 ሜትር ገባ ብሎ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 011 156 5095 መደወል ይችላሉ።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ
04 ፋይናንስ ፅ/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Catering and Cafeteria Services cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Freight Transport cttx, cttx Hospitality, cttx Hotel Service Provision cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Rent cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Tents and Camping Equipment cttx, cttx Textile, cttx Tour and Travel cttx, cttx Transportation Service cttx, cttx Vehicle cttx, cttx Warehousing, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Tour and Travel cttx, Transit and Transport Service cttx