Your cart is currently empty!
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ያገለገሉ ንብረቶችን፣ ወረቀቶችን እና ካርዶችን በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 02, 2026)
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ያገለገሉ ንብረቶችን፣ ወረቀቶችን እና ካርዶችን በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ንብረቶቹን በጤና ጣቢያው በመገኘት ማየት እና የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ለየምድቦቹ (ሎቶች) የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በካሽ ወይም በCPO ማስያዝ አለባቸው።
- ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በዋጋ መሙያው ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ከፍለው ንብረቶቹን በ3 ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው።
- ለጨረታው አሸናፊዎች ካሸነፉበት ንብረት ዋጋ ላይ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተቀናሽ ይደረግላቸዋል፡፡ በጨረታው ለሚሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ7ኛው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ
ስልክ ቁጥር 0111-12 94 72
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሰሜን ጤና ጣቢያ