የኅብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ ዕቃዎች፣ የትምህርት መማሪያ እቃዎች፣ የደንብ ልብስና የስፖርት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ቋሚ እቃዎች እንዲሁም የልብስ ስፌት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 03/2018

በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የኅብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግዥ ለመፈፀም ስለሚፈልግ በዚህም መሰረት ፡-

  • ሎት-1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ ዕቃዎች።
  • ሎት-2. የትምህርት መማሪያ እቃዎች፣  የደንብ ልብስና የስፖርት እቃዎች።
  • ሎት-3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ቋሚ እቃዎች።
  • ሎት-4. የልብስ ስፌት።
  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችው በመስኩ ሕጋዊ ሰነድ እና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የሆኑና ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ሙሉ ስነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና አድራሻ መፃፍ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የኅብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ኅብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ጠዋት4፡30 ኅብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣2፣4 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 3 በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  9. የጨረታ አሸናፊ ከተቋሙ ጋር ውል ለመዋዋል በቅድሚያ የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ አለበት።
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ፒያሳ ከመብራት ኃይል ወደ እሪበከንቱ በሚወስደው መንገድ ጎጀብ ጥርስ ሕክምና ጎን
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-1-26-64-18 / 09-12-85-03- 39/09-11-38-31-11 ይደውሉ።
የኅብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት