Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባምንጭ ሪጅን የተለያዩ የማይሰሩ የዲዝል ጄነሬተሮች እና መለዋወጫ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር –ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ-5653/100/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባምንጭ ሪጅን ከታች የተዘረዘሩ የተለያዩ የማይሰሩ የዲዝል ጄነሬተሮች እና መለዋወጫ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ የብረታ ብረት አቅላጭ ፋብሪካ ተጫራቾች ብቻ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
|
ሎት ቁጥር |
ተ.ቁ |
የሚወገደዉ የዕቃው ዓይነት |
ንብረቱ ያለበት ሁኔታ |
መለኪያ
|
ብዛት
|
የጨረታ መነሻ የአንዱ ዋጋ ከተ/ዕ/ታ በፊት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታው መዝጊያ ቀን |
የጨረታው መክፈቻ ቀን |
|
ሎት– 1
|
1 |
ዳትሱ 688 ኬቪኤ ዲዝል ጄነሬተር |
የማይሰራ |
በቁጥር |
1 |
910,885.50 |
150,000.00 |
የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 |
የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
|
2 |
ዲዩዝ 170 ኬቪኤ ዲዝል ጀነሬተር |
የማይሰራ |
በቁጥር |
1 |
425,079.90 |
||||
|
3 |
ዲዩዝ 188 ኬቪኤ ዲዝል ጀነሬተር |
የማይሰራ |
በቁጥር |
1 |
425,079.90 |
||||
|
4 |
ከሚንስ 1250 ኬቪኤ ዲዝል ጀነሬተር |
የማይሰራ |
በቁጥር |
1 |
469,612.08 |
||||
|
5 |
የከሚንስ 1250 ኬቪኤ እና የዳትሲ 688 ኬቪኤ ጄነሬተሮች አካላት |
የማይሰራ |
በቁጥር |
3 |
65,887.00 |
||||
|
6 |
የዳትሱ ጄነሬተር መለዋወጫዎች |
New/Use d/Scrap |
በቁጥር |
45 |
195,239.00 |
||||
|
7 |
የድዩዝ ጄነሬተር መለዋወጫዎች |
New/Use d/Scrap |
|
11 |
57,729.00 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ የብረታ ብረት _አቅላጭ ፋብሪካ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ዝርዘር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር 1000255391422 የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ስዓት አርባምንጭ ሴቻ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባምንጭ ሪጅን ቢሮ ቁጥር 301 በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የብረታ ብረት አቅላጭ ፋብሪካ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 046-181-5412 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባምንጭ ሪጅን