የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሆኑ የተለያዩ ንብረቶች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ መሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር PPS/NVP‐1FBI/06/05/2018

የኢ... የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሆኑ የተለያዩ ንብረቶች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላል፡፡

1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ተጫራች በኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ አወጋገድ ከፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በዘርፉ ፈቃድ የተሰጠው ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ፈቃድ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ... የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ በመምጣት የንብረቶች ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ በቴሌ ብር እና ሲቢኢ ብርን በመጠቀም የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ከላይ በተጠቀሱት /ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000/መቶ ብር ያልበለጠ ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

6. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 415 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም፡፡

7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::

8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡

11. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ የኢ... የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት

ለበለ መረጃ፡የተቋማችንን ድህረገጽ www.pps.gov.et ይጎብኙ

የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት /አዲስ አበባ/


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *