Your cart is currently empty!
የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት፣ በስፖርት ም/ቤት በጀት እና በሰቆጣ ቃልኪዳን ድጋፍ ገንዘብ የአቅርቦት ግዥዎች ለመፈፀም ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት፣ በስፖርት ም/ቤት በጀት እና በሰቆጣ ቃልኪዳን ድጋፍ ገንዘብ የአቅርቦት ግዥዎች
- ሎት1. የውሀ ተቋማት የግንባታ ቁሳቁስ አቅርቦት ግዥ፣
- ሎት2. የስፖርት ቁሳቁስ እና መገልገያዎች አቅርቦት ግዥ፣
- ሎት3. የስፖርት አልባሳትና ጫማዎች አቅርቦት ግዥ፣
- ሎት4. የንጽህና መጠበቂያ እና ኮስሞቲክ እቃዎች አቅርቦት ግዥ፣
- ሎት5. የአትክልትና ፍራፍሬ ዘር አቅርቦት ግዥ፣
- ሎት6. የመዝናኛ እና የሙዚቃ መሳሪያዎች አቅርቦት ግዥ ለመፈፀም
በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአቅርቦት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1. 30,000 (ሰላሳ ሽህ)፣ ብር ሎት2. 2,000 ( ሁለት ሽህ) ብር፣ ሎት3. 5,000 (አምስት ሽህ) ብር፣ ሎት4. 2,000 (ሁለት ሽህ) ብር፣ ለሎት5. 2,000.00 (ሁለት ሽህ ) ብር፣ ለሎት6. ብር 2,000.00 (ሁለት ሽህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እንዲሁም ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በደረሰኝ በማስያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ወይም ከዋጋ መሙያ ሠነዳቸውጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው በተሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ ሲሆን ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸውም ነገር ግን ስርዝ ድልዝ ካለበት ራሳቸው የሰረዙት ለመሆኑ ፓራፍ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋጋውን በመሙላት የተጫራቹ ስም፣ ፊርማ፣ ማህተምና ሙሉ አድራሻ እና የጨረታ ማስከበሪያ፣ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀትና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎችን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ፖስታው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ 15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በተራ ቁጥር 8 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በአሸነፈበት የአቅርቦት ግዥ ውል በመፈፀም አቅርቦቱን መፈፀም ይጠበቅበታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በየሎቱ ጥቅል ድምር አሸናፊውን የሚለይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደም/ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 773 02 74 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Art cttx, cttx Audio Visual, cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Music and Entertainment cttx, cttx Musical Instruments cttx, cttx Personal Care Products and Services cttx, cttx Products and Services cttx, cttx Raw Materials and Supplies cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Sport Materials and Equipment cttx, cttx Textile, cttx Water Pipes and Fittings cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Photography and Filming Service and Equipment cttx