የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የትራክተር መኪና በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 05, 2026)

አንደኛ ደረጃ ሀራጅ ማስታወቂያ

የአፈ/ ከሳሽ —— የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአፈ/ተከሳሽ —– አቶ ሃድሽ ብርሃኔ መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ከስ ጉዳይ /ቤት ጥር 19 ቀን 2018 . : በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአፈ/ተከሳሽ እንደፍርዱ ሊፈጽሙ ባለመቻላቸው ምክንያት በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መጋዝን ውስጥ ታግዶ ያለው የሻንሲ ቁጥር E411C6Y026500 ሞተር ቁጥር NM75424U254989A ሞዴል አርማህ 110 የፈረስ ጉልበት የሆነ ትራክተር መኪና ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በመነሻ ዋጋ ብር 4,600,000 / አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ብር / በሆነ መነሻ ዋጋ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ በአንደኛ ደረጃ የሐራጅ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከጥር 28 ቀን ጀምሮ ታትሞ እንዲወጣ /ቤቱ አዟል፡፡ በመሆኑም ከላይ የተገለፀውን : ትራክተር መኪና መጫረት (መግዛት) የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ሁሉ መኪናው ካለበት አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ የኢት/ልማት ባንክ መጋዘን ውስጥ ሂዳችሁ በማየት የካቲት 30 ቀን 2018 / ከጠዋቱ 300 እስከ ቀኑ 600 ሰዓት ድረስ በአማራ ክልል ማአከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመቅረብ መጫረት እና መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንድታሟሉ እየገለጽን፣

1. ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 300 ሠዓት እስከ ቀኑ 600 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መኪናውን አይቶ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ገዥ ሲያሸንፍ አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ያስይዛል

3. ገዥ ሲያሸንፍ 15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከከፈለ ስመንብረቱ ወዲያውኑ እንዲዛወርለት ይደረጋል፡፡

4. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ወቅት መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. በጨረታ የሚወዳደሩ ራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው ይሆናል።

6. በጨረታ ወቅት ሁከት የሚፈጥር በህግ ይጠየቃል፡፡

7. ስመ ንብረት ማዛወሪያ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡

8. ጨረታው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐራጅ ባይ የሚመራ ይሆናል።

ከዚህ በላይ በዝርዝር የቀረበውን የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ አሟልታችሁ ለመወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ በአካል ቀርበው በጨረታው ቀን እና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣ የማዕጎን/ዞን ከፍ//ቤት አዟል ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *