Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ አገልግሎት የሰጡ አስር (10) ተሽከርካሪዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር/EEP/DS/05/18
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል።
- ሎት1 ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ አገልግሎት የሰጡ አስር (10) ተሽከርካሪዎች ኮተቤ አካባቢ ብረታ ብረት ፊት ለፊት የሚገኘው የተቋማችን ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ፣ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕለይ ስቶር። (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።
1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሰ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።
2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንበረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ሥር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነፃ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት የተቋሙ ጣቢያዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል።
4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ሲፒኦ በማሰራት ወይም ደግሞ በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ሲፒኦ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይቻላል።
7. ጨረታው ከ05/06/2018 ዓ.ም እስከ 20/6/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ይካሄዳል። ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (Online) መከታተል ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia ) ብለው በማውረድ ወይም (Auction.et) ላይ መመዝገብና መጫረት ይችላሉ።
9. በጨረታው አሸናፊው ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፋችሁበትን ዋጋ ሙሉ ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን የሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈፀም ግዴታ ይኖርባቸዋል። ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለውድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል።
10. ከላይ የተጠቀሰውን አና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራቾች ከጨረታው ውድቅ ሊሰረዝ⁄ ይችላል።
11. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር፡- 09-0511-5511/011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
13. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር፡- 011-558-14-24 ወይም 011-558-06-49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል