በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ማቴሪያሎችን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ማቴሪያሎችን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 07, 2026)

የሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ማቴሪያሎችን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

  • ሎት1 ፦አሸዋ በቢያጆ፤ ጠጠር 02 በማሽን የተፈጨ በቢያጆ፤ የፍልጥ ድንጋይ በቢያጆ፤ የሙሉት ድንጋይ በቢያጆ
  • ሎት2፡ የህንፃ መሣሪያ ግዥ
  • ሎት3፡፤ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ፤
  • ሎት4፡ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፤
  • ሎት 5፡- አጠና ግንድላና ባህር ዘር ዛፍ ግዥ

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ተሻሽለዉ በወጣው በመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 ዓ/ም መሰረት፡-

1. የ2018 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ፤

2. የዘመኑ ግብር የከፈሉበት መረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር/Tin Number/ያላቸዉ፤

4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነበት መረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፤

5. ከሽያጭ ዋጋ ላይ ለመንግስት ግብር 3% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤

6. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

7. የዕቃ አቅራቢነት በኦንላይን የተመዘገበበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

8. የጨረታ ሁኔታ በአይቴም ወይም በጥቅልል ሊሆን ይችላል፤

9. የጨረታዉን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት ኦርጂናሉንና ኮፒዉን የጨረታ ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ ዉስጥ በማስገባት በሰም በታሸገዉ ኤንቨሎፕ ፖስታ ዉስጥ በማድረግ በቁጫ አልፋ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ 5 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀዉ ጨረታ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፤

10. በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የዉል ማስከበሪያ 20% ማስያዝ ግዴታ አለባቸዉ ፤

11. ጨረታዉ በአየር ላይ የሚቆየዉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት / ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።

12. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ወደ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋ/ፕ/ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር-5 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናሉ።

13. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በጥሬ ወይም በቼክ 20,000.00/ ሃያ ሺህ ብር ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ህጋዊ CPO/ ከሚሳተፉበት ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ግደታ አለባቸው ፤

14. የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው የጨረታ ማብቂያ በ15ኛዉ ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት ይሆናል፤

15. ጨረታው የሚከፈተዉ በ16ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፤

16. በጨረታዉ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃዉን እስከ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ አዉራጅ እና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

17. ተጫራቾች ወይም የጨረታ ወኪል ያለመገኘት ጨረታዉን መክፈት አያስተጓጉልም፤

18. የ16ኛዉ ቀን ሰንበት ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤

ማሳሰቢያ፡-

በጨረታዉ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ የዕቃዉ ከጥራትና ደረጃ ዝቅ ቢል ፣ዕቃዉ ቢጎድል ከተዋወለዉ ከውሉ ጊዜዉ ብያልፍ በህግ መሰረት ለመንግሥት ከገባሁት ከጠቅላላ ውል ገንዘብ ላይ 20% ያህሉን የሚደርሰዉን ብር ተቀጥቼ ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ በፍ/ህ/ቁጥር 2005 መሰረት የፀና ይሆናል ፡፡

  • ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት በህግ የተጠበቀ ነዉ ፤ ለበለጠ መረጃ ስልክ 0926 366 087 /0976 135 648/ 0984 666 189 ደውለው ይጠይቁ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *