የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦቲ ጫማ የወንዶች እና የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦቲ ጫማ የወንዶች እና የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን 2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦት ጫማ የወንዶች እና የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣

1. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል 15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የስራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ፤የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበትን እቃ ዋጋ ብር 150,000.00/አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡

5. የቴክኒካል ሰነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. የጨረታ ሰነድ 24/7/2018 ቀን እስከ 13/08/2018 .. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተደረር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 14/08/2018 .. ከጠዋቱ 300 ሣጥኑ ታሽጎ 3.30 ሠዓት ይከፈታል፡፡

8. ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55/0251-11-37-43 በመደወል መረጃ ..ቁጥር 1453 ማግኘት ይችላሉ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *