Be'kur (Apr 06, 2026)
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የ2016 እና የ2017 በጀት ዓመት ሂሳብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱን ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ደረጃ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የሙያና የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ፡፡
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጭው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጲያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማሕበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የበጀት ዓመቶች ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ በሰጠው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያከናውኑት ተግባር ከድርጅቱ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈራረም ፈቃደኛ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ስለ መልካም ስራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) ካደረጉባቸው ድርጅቶች የተፃፈላቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት (ተመዝጋቢ ከሆነ)፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት (ቲን) እና ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) ጎንደር ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከመጋቢት 28/2018 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 12/2018 ዓ/ም በሥራ ሰዓት በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመግዛት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክስን ጨምሮ) በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ቢሮ ቁጥር 14 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የበጀት አመቱን ኦዲት ሥራ፣ የኦዲት ሥራው የሚከናወንበትና የሥራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚያቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወሰድባቸውን ጊዜ በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር (ማስኬጃ ውል/ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ሚያዚያ 13/2018 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 14 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ 16ኛው ቀን በዓል (የእረፍት ቀን) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ በአገር አቀፍ በዓላት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 የስራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የስራ ቀን ይቆጠራል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 111 04 59 ወይም 058 211 33 16 በመደወል ያነጋግሩ ፋክስ 058 111 43 72 መላክ ይችላሉ፡፡
የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት