Reporter (Apr 08, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ሲዳማ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በሲዳማ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ::
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል:: በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ወይም ቼክ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል::
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል::
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዛወሪያ እና ማናቸውም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል:: ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል:: ሌላ ውዝፍ ዕዳ ካለ ከባንኩ ዕዳ የሚተርፍ ገንዘብ ሲኖር ባንኩ የሚከፍል ይሆናል::
- ተሽከርካሪውን በሥራ ሰዓት በአካል መመልከት ይቻላል::
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል::
- የጨረታው ቦታ ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው በባንኩ ሕንጻ 6ኛ ፎቅ የሕግ ክርክርና ፎርክሎዤር ዲቪዥን ይሆናል::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 221 8625 / 0114 706 408 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
|
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የተሽከርካሪው መግለጫ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
ጨረታው የወጣው |
|||||
|
የተሽከርካሪው ዓይነት |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ |
ስሌዳ ቁጥር |
የተሰራበት ዘመን |
ሻንሲ ቁጥር |
ሞተር ቁጥር |
|||||||
|
አቶ አለማየሁ ወንጫኖ ወሼ |
ተበዳሪው |
ቶዮታ ሃይሉክስ ደብል ገቢና |
በሲዳማ ባንክ አ.ማ ሀዋሳ ዲስትሪክት ግቢ ውስጥ |
AA-03- B46358 |
2022 G.C |
MR0BA8 CD0N0238927 |
1GD- 5156358 |
13,379,850.00 |
ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም |
3:00-4:00 |
4:00-5:00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |