2merkato.com (Apr 13, 2026)
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤት
(በሬድዮ እና በቴሌቭዥን የሚነበብ)
የ1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤት ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁና በቆዬ ፈጬ፣ በቡራዩ፣ በመልካ ኖኖ እና በፉሪ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ቴሌብር (telebirr) በመጠቀም shaggarland.2merkato.com ወይም shaggarland.afrotender.com ድረ-ገጾች ላይ በመግባት በኦንላይን መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሰነድ ግዢውን ከሚያዝያ 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት መፈፀም ይችላሉ፤ ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ (CPO)፣ የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ ሰነዱን ለመግዛት የከፈሉበትን የቴሌብር ደረሰኝ ወይም ስሊፕ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በፖስታ (በኤንቨሎፕ) በማሸግ እስከ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ንፋስ ስልክ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወይም ጎተራ ማሞ ኮንዶሚኒየም አካባቢ የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤት በሚገኝበት የሸገር ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት (MESOB) ህንፃ ምድር ቤት (በጉግል ቦታ ማሳያ) https://maps.app.goo.gl/toCJZwKSxr2Sxckv7?g_st= ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 3 የስራ ቀናት መስሪያ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ ባዘጋጀው ቦታ ላይ የሚከፈት ሆኖ፣ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃው በማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሚያዝያ 08/2018 ዓ.ም በወጣው ከለቻ ኦሮሚያ እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሱት ድረ ገጾች መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በመሬት ጽ/ቤቱ ስልክ ቁጥር +251-11-47-095-44 ወይም +251-11-47-080-06በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት፡ እዚህ ይግቡ