የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የእንስሳት መኖ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የእንስሳት መኖ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 13, 2026)

ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

NCB 003/2018

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የቀረበውን ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ NCB 003/2018 አወዳድሮ የእንስሳት መኖ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ በመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ቲን ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተቀመጠው ቀንና ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 20,000.00 (ሃያ ብር) በባንክ የተመሰከረለት .. ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናልና በአንድ ኢንቨሎፕ ታሽጎ ኮፒ ተደርጎ መቅረብ አለበት:: የኮፒ ሠነዶች ከኦሪጅናል ሠነዱ ጋር በአይነትም ሆነ በብዛት ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡የጨረታውን ስምና ቁጥር በመግለጽ በኮርፖሬሽኑ ግዥ ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 530 ተዘግቶ ከረፋዱ 545 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው /ቤት ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

6. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር /011-517-25-21/11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *