በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ ነጭ በቆሎ እና ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ ነጭ በቆሎ እና ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Be'kur (Apr 13, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ የ2018/2019 ምርት ዘመን ለሁለተኛ ጊዜ

  • ሎት 1. 5000 ኩ/ል ነጭ በቆሎ
  • ሎት 2. 5000 ኩ/ል ነጭ በቆሎ የወጣ እና ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ
  • ሎት 3. 5000 ኩ/ል ስንዴ የ2018 ምርት ዘመን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሰለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ ዲቪጂን በመውሰድና ዋጋ ሞልተው በማሸግ ፖስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ላይ የሚቆይ ሲሆን እስከ 8ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እና በ8ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በእለቱ በ8ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም፡፡
6. ተጫራቾች በኢትዮጲያ በሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
8. አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጠበት ቀን ጀምሮ በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ
ማስገባትና ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ካላደረጉ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
9. የማንሻ ቦታ ቡሬ ከተማ 04 ቀበሌ የሚገኘው መጋዝን ሲሆን የመጫኛና ልዩ ልዩ ወጭዎችን ገዥ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
10. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተገለጹ ነገሮችን ቢኖሩ በዩኒኑ ግዥ እና ሽያጭ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
11. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 98 በመደወል ወይም በአካል በመገኝጥ መስተናገድ ይችላሉ፡፡
13. ማንኛውም ተጫራች የመንገድ እና የቀረጽ ወጭዎችን መሸፈን የሚችል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀንና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *