ጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ኤልክትሮኒክስ ነክ /ሞባይሎች/፣ ኮስሞቲክሶች፣ ጫማ ነክ፣ እና አልባሳት ነክ እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ኤልክትሮኒክስ ነክ /ሞባይሎች/፣ ኮስሞቲክሶች፣ ጫማ ነክ፣ እና አልባሳት ነክ እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 15, 2026)

ሶስተኛ ጊዜ የወጣ የግጽ ጨረታ ማስታወቂያ

1. ጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው በጅማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚገኙ

  • የተለያዩ ኤልክትሮኒክስ ነክ/ሞባይሎች/ ኮስሞቲክሶች፣ ጫማ ነክ፣ እና
  •  አልባሳት ነክ እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎች

ባሉበት ሁኔታ ሚያዝያ 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በጅማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:

1. በቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን በጨረታ በቀረቡት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ነክ/ሞባይሎች ኮስሞቲክሶች፣ ጫማ ነክ፣ እና አልባሳት ነክ እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር ተጫራቾች በዘርፍ የፀናና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ክሊራንስ) በማቅረብ መወዳደር የሚችል፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11/8/2018 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በጅማ/ጉ/ቅ/ጽ/ቤት እና ከሆሌ ጉ/መቆጣቢያ የጨረታ ሠነድ በመግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) 5% ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ በጅማ ጉ ቅ/ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን ማስታወቂያ ከወጣበት ከቀን 7/8/2018  እስከ 11/8/2018 ዓ.ም.

የጨረታ የመዝጊያና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ጅማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት

ሐራጅ ጨረታ

ሚያዝያ 12/2018 ዓ.ም 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ በጅማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ላይ ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-211-62-87-047 211 29-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ጅማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት