Be'kur (Apr 13, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጎሕ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ
- ሩዝ ቀይ እና ነጭ ያልተመሸነ ብዛት 5372 ኩ/ል፣
- ጤፍ 3409 ፣
- ስንዴ ብዛት 182 ኩ/ል፣
- የቢራ ገብስ 464 ኩ/ል፣
- የጥራጥሬ እህል ብዛት 495 እና
- የቅባት እህል/ኑግ 286 ኩ/ል በድምሩ 10208 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚታሟሉ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. በዚህ ንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ጎሕ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎህ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ገዝቶ በመውሰድ የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣
ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትን ሰነዶች አሟልተው እና ዋጋቸውን ሞልተው በፖስታ በማሸግ ከዩኒዬኑ ቢሮ ደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ጨምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ7ኛው ቀን መጨረሻ 8፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
6. የምርቱን ናሙና ማየት ለሚፈልጉ ደ/ታቦር ነ/መውጫ እና ይፋግ ከሚገኘው ከዩኒየኑ መጋዝን ማየት ይችላሉ፡፡
7. አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ ከፍተኛ ዋጋ የሞላ /ያቀረበ/ ሲሆን አሸናፊው በተለየ በ5 ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪ የጠቅላላ የዋጋውን 10 በመቶ ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ዩኒዬኑ ያወጣውን የጨረታ ማስታወቂያ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. አሸናፊ ምርቱን የሚረከበው ከዩኒዬኑ መጋዘን ሲሆን የትራንስፖርት እና የወዛደር ወጭ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
10. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጎሕ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተወሰነ