የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መልካዲዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣ ቴሌቪዝኖች፣ የተለያዩ የውሃ መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መልካዲዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣ ቴሌቪዝኖች፣ የተለያዩ የውሃ መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 22, 2026)

ዕቃዎችን ለመሸጥ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ መልካዲዳ/ስተአ/001/2018

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መልካዲዳ ቅርንጫፍ /ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣ ቴሌቪዝኖች፣ የተለያዩ የውሃ መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልገ ማንኛውም ተጫራች፡

1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መልካዲዳ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መልካዲዳ ቅርንጫፍ /ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሚያዝያ 14/2018 / ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 27/2018 . ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ / CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3) ማንኛውም ተጫራች ከሚያዝያ 14 እስከ ሚያዝያ 27/ 2018 . ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መልካዲዳ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ መልካዲዳ ቅርንጫፍ /ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል።

4) ጨረታው መልካዲዳ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ መልካዲዳ ቅርንጫፍ /ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሚያዝያ 27 ከቀኑ 830 ታሽጎ በዕለቱ ሚያዝያ 27 ከቀኑ 900 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡

5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያሰያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያሰያዙት የጨረታ ዋሰትና 3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

6) ተጨራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።

7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራቾች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 965 725 833 0912 487 328 ወይም +251 954 779 317 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት