Reporter (Apr 22, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 9/2018
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
- የጥበቃ አገልግሎት ግዥ፣
- የውሻ መኖ ማሸጊያ ኘላስቲክ፣
- LAPTOP ግዥ፣
- በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሞተር ሳይክል፣
- ዲፕ ፍሪጅ ከ1200ኪ.ግ – 1600ኪ.ግ for storage of cattle፣ ከ250-300ኪ.ግ for storage of Beef Feet፣
ማንኛውም ተጫራች፡-
- በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር(TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3ዐ ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል፣
- የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
- ጨረታው ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡3ዐ ሰዓት የጨረታ ኮሚቴዎች፣ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ11466-47-05 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት