የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንጋ ዲስትሪክት ኮምባይነር (Combiner Brand: Kubota Country of Origin China) አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንጋ ዲስትሪክት ኮምባይነር (Combiner Brand: Kubota Country of Origin China) አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 23, 2026)

የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንጋ ዲስትሪክት ስምና አድራሻው ከዚህ በታች የተገለፀውን ተበዳሪ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡው የመያዣ ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባለበት ሁኔታ በድርድር አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

.

ተበዳሪው መያዣ ሰጪው/ስም

ንብረቱ ፕሮጀክቱ/ የሚገኝበት አድራሻ

የሚሸጠው የንብረት አይነት

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)

የድርድር ሽያጩ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት

ሐራጅ ሚካሄድበት ቦታ

የድርድር ሽያጩ ሂደት

1

ተኬ እና አና አግሮ ኢንደስትሪ /የተ/የግ/ማህበር

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ

ኮምባይነር (Combiner Brand: Kubota Country of Origin China)

3,161,747,33 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ሰባት መቶ አርባ ሰባት 33/100 ሳንቲም

ግንቦት 13 ቀን 2018 . 400 እስከ 600 ሰዓት

በቦንጋ ዲስትሪክት

3 የድርድር ጨረታ

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ተኛ (አንድ አራተኛ) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በማስያዝ የድርድር ሽያጩ ላይ መሳተፍ ይቻላሉ።

2. ተደራዳሪዎች(ተጫራቾች) የዋጋ ማቅረቢያ ማመልከቻ ላይ ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልፅ በመፃፍ እስከ ግንቦት 4 ቀን 2018 . ከቀኑ 1000 (ሰዓት) ድረስ በቦንጋ ዲስትሪክት /ቤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15/አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ነገር ግን ንብረቱን ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃሎ ገቢ የማያደረግ ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የድርድር ሽያጩ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሜ ለድርድር ጨረታ ሲቀርብ የዋጋ ልዩነት ከተፈጠረ ልዩነቱን ይጠየቃል።

4. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በቦንጋ ዲስትሪክት /ቤት ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው በመገኘት ሂደቱን መከታተል ይችላሉ።

5. አሸናፊው ተጫራች ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

6. የጨረታው አሸናፊ ንብረቱን በገዛው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸውበሕግ የተወሰኑ ቀረጥና ግብር እንዲሁም የስም ማዘዋወሪያ ይከፍላል.

7. ንብረቱ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለበት ስለሆነ ገዢው የቀረጥ ነፃ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ ታክስ ለመንግስት ለመክፈል ይገደዳል።

8. ባንኩ ለሽያጭ የቀረበውን መያዣ ንብረት የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ወይም አሸናፊው በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።

9. ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚፈልግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንጋ ዲስትሪክት፤ ስልክ ቁጥር 047-331-1992 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

10 ለድርድር ሽያጭ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም የድርድር ጨረታ ተሳታፊ ጅማ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት በመቅረብ መጎብኘት ይችላል።

11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የድርድር ሽያጩን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንጋ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *