Addis Zemen (Apr 23, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 23/2018
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ
- የተለያዩ ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች፣
- አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣
- የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣
- ስፔርፓርት ዘርፍ እቃዎች፣
- ምግብና መጠጥ ዘርፍ እቃዎች እና ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች በግልጽ ጨረታ
እንዲሁም
- ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች፣
- አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣
- ልዩልዩ እቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣
- ጌጣጌጥ ዘርፍ እቃዎች፣
- ስፔርፓርት ዘርፍ እቃዎች እና
- የጽዳት ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 23/2018 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸዉ ለሀራጅ ጨረታ በጨረታ መከፈቻ ቀን ይዘዉ መቅረብ አለባቸዉ።
2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋዉ ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠዉ እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛዉም እድሜዉ ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጲያዊ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገዉ በጨረታዉ ሊሳተፍ ይችላል።
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ እቃዉን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካዉንት ቁጥር 1000296553216 በኃላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ፣ በተራ ቁጥር 1 ከተገለጹት እና ሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና ፊርማ በግልጽ በመጻፍ እስከ ጨረታዉ መዝጊያ ቀን 22/08/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሃደት ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
4. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር)፣ ለአልባሳት ዘርፍ እቃዎች ብር 51,000 (ሃምሳ አንድ ሽህ ብር)፣ ለልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 15,500 (አስራ አምስት ሽህ አምስት መቶ ብር)፣ ለምድብ 5 ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች ብር 20,623 (ሃያ ሽህ ስድስት መቶ ሃያ ሶስት ብር)፣ ለምድብ 6 ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች ብር 43,000 (አርባ ሶስት ሽህ ብር)፣ ለጌጣጌጥ ዘርፍ እቃዎች ብር 1,502 (አንድ ሽህ አምስት መቶ ሁለት ብር)፣ ለስፔርፓርት ዘርፍ እቃዎች ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) እና ለጽዳት ዘርፍ እቃዎች ብር 14,000 (አስራ አራት ሽህ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በቀጥታ አካዉንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 22/08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ መገኘት አለባቸው።
5. ከላይ በተራ ቁጥር 3 እና 4 በተገለጸው መሠረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።
6. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ የሰጠዉን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ራሱን ከዉድድር ዉጭ ማድረግ አይቻልም።
7. ለግልጽ ጨረታ ከጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸዉም።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6:00 ሰዓት ከሰዓት በኃላ ከ9፡00-12፡00 የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22/08/2018 ጠዋት 3፡00 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሃደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ።
9. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 22/208 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00 6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኃላ ከ9፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00 6:00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ።
10. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 22/08/2018 ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ |
በ22/08/2018ዓ.ም ከጠዋት 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 3፡40 ሰዓት ይከፈታል |
|
2 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
ሀራጅ ጨረታ |
እስከ 22/08/2018 ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ |
በ22/08/2018ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
11. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል። ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጂናል ይዘዉ መቅረብ አለባቸዉ።
12. በጨረታ ለሚሽጥ እቃ የጨረታ ዉጤት እንደተገለጸ ከአሸናፊው ጋር የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል።
13. ምድብ ለወጣላቸው ሀራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ ድምር ከፍተኛው ዋጋ ይሆናል። በተጨማሪም ተጫራቾች በምድቡ ለቀረቡት ለእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ መስጠት አለባቸው።
14. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል።
15. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
16. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ የመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል።
17. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመሥሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊዉ የአሸነፈበትን የአቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
18. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታዉ መሳተፍ አይችሉም።
19. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች የሚገኙበት ቦታ ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሆኑ ይታወቅ።
20. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተደደር የሥራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033 559 0114 ደውለውመጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት