Addis Zemen (Apr 24, 2026)
ለኦዲት ስራ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን እ.ኤ.አ. ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት መር የሆነ የድጋፍና እንክብካቤ ወላጅ የሌላቸውና አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ሕፃናት እያደረገ የሚገኝ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን፣ እንዲሁም በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ እንደገና የተመዘገበ ነው።
በዚሁ መሰረት፡– ድርጅታችን እ.ኤ.አ. በ2025 የበጀት አመት የፈፀመውን የስራ ክንውኖችንና ሂሳብ ሰነድ በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል። ድርጅቱ እንዲመረምርለት ያቀረበው የቦክስ ፋይል ብዛት በቁጥር 20/ሃያ/ ሲሆን፣
ለመወዳደር የሚፈልግ ኦዲተር/ የኦዲት ፈርም የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላት አለበት።
1. የኦዲተርነት የሙያ ማረጋገጫያለው/ያላት
2. የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
3. የዘመኑን ግብር ስለ መክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው/ያላት
5. ከፌዴራል ወይም ክልል ኦዲተር መስሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችል/የምትችል/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችንና የምትሰሩበትን ዋጋ የያዘ ሰነድ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ፡ +251979 335334/ 0926506017
አዲስ ተስፋ ማዕከል ለህፃናትና አካል ጉዳተኞች