በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ለመኖርያ፣ ንግድና ለቢዝነስ ማዕከልነት አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል – test3.diretenders.com

በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ለመኖርያ፣ ንግድና ለቢዝነስ ማዕከልነት አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል


Yedebub Nigat (Apr 25, 2026)

የመሬት ሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ

በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት /ቤት በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ለመኖርያ ንግድና ለቢዝነስ ማዕከልነት አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል።

ስለሆነም፡

1. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በግንባር በመቅረብና የማይመለስ ብር 900/ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ፡፡የሰነድ ሽያጩ እስከ አስረኛው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 9.00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይከናወናል።

2. ተጫራቾች ቦታውን በሊዝ ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ፣የሚጫረቱበትን ቦታ መለያ ቁጥር /ኮድ/፣የቦታውን ስፋትና የሚሰጠውን አገልግሎት በመጥቀስ በጨረታው ሰነድ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትናው መጠን፣የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ ያላነሰ ሆኖ ከህጋዊ ባንከ በስሙ የተሰራና ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የባንክ አካውንት ቁጥር 1000029392227እንዲከፈል የታዘዘ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ከመልስ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ አስረኛው የስራ ቀን 1055 ሰዓት ድረስ ሀላባ ከተማ ማዘጋጃ ቤቱ ቢሮ ዘንድ በግንባር በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አስመዝግቦ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ 11.00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል።

3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ በሚኖረው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት በማዘጋጃ ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ሆኖም ተጫራቻቾ ካልተገኙ ጨረታው የሚከናወን ይሆናል።

4. የጨረታ አሸናፊዎች ውጤቱ በተገለፀላቸው መሰረት በአስር የስራ ቀናት ውስጥ በማዘጋጃ ቤቱ በመቅረብያ ሸነፉበትን ዋጋ ቅድመ ክፍያ በመክፈል ውል መፈጸም ያለበት ሲሆን ይህን ካልፈፀመ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይፃፍበታል፤ማስጠንቀቂያው ከደረሰው 3 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውሉን ሳይዋዋል ከቀረ አሸናፊ መሆኑ ይሰረዛል፣ለጨረታ ማስከበሪያ አስይዞት የነበረውም ገንዘብ ለከተማ አስተዳደሩ ገቢ ይሆናል።

5. አንደኛ የወጣው ተጫራችው ልካልፈፀመ ሁለተኛ ለወጣው ተጫራች አንደኛ የወጣው ባሸነፈበት ዋጋ ለመውሰድ ከፈለገ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ እንዲወስድ ይደረጋል፡፡ሆኖም ሁለተኛ የወጣው ተጫራች ከፍሎ ለመውሰድ ፈቃደኛ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ በድጋሜ ይወጣል።

6. በመመዘኛዎቹ መሰረት እኩል የወጡ ተጫራቾች ካሉ አሸናፊውን የመሬት ጨረታ ኮሚቴው በጨረታ ውጤቱ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋና የገቧቸው ግዴታዎች ተመሳሳይ ሆነው ከመቶ እኩል ነጥብ ካገኙና ከውድድሩ ተካፋዮች ውስጥ ብቸኛ ሴት ተወዳዳሪ ካለች የጨረታው አሸናፊ እንድትሆን ይደረጋል፡፡ከዚህ ውጭ ከሆነ አጠቃላይ አሸናፊው በዕጣ እንዲለይ ይደረጋል።

7. ተጫራቹ ቅድመ ክፍያውን አጠናቅቆ ከከፈለ በኋላ ከማዘጋጃ ቤቱ ጋር የሊዝ ውል በመፈራረም ፕላኑ በሚፈቅደው መሰረት የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ መርሃግብር አዘጋጅቶ በማቅረብ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬትና ቦታውን ይረከባል።

8. ቦታውን ለመግዛት የሚወዳደሩት ተጫራቾች ቁጥር ከሦስት ማነስ የለበትም፡፡ሆኖም በጨረታው የተሳተፉት ተወዳዳሪዎች ቁጥር ከተጠቀሰው መጠን በታች ከሆነ ጨረታው ተሰርዞ እንደገና ማስታወቂያ እንዲወጣበት ይደረጋል።

9. ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግላቸው ሲሆን አፈፃፀሙም ጨረታው ከተከናወነ በኋላ ካለው የስራ ቀን ጀምሮ ይሆናል።

10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቦታ በአካል ተገኝተው መጎብኘት ወይም በፕላን መልክ መመልከት ከፈለጉ ከጨረታው ቀን በፊት በጨረታ ኮሚቴ አስጎብኝነት ቦታውን ማየትይችላሉ።

11. ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

12. በጨረታ ውህጋዊ የሆነ የማንኛው ሀገር ዜግነት ያለው መወዳደር ይችላል።

13. ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በአሃዝና በፊደል መግለፅ አለባቸው፡፡ ሆኖም የአሃዝና የፊደል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው የገንዘብ መጠን ገዥ ይሆናል።

15. በጨረታ ኮሚቴ የተሰረዘበት ተጫራች ቅሬታ ካለው 5 የስራ ቀናት ውስጥ ለማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ማቅረብ ይችላል፣

16. ተጫራቾች ጨረታውን ለማሸነፍ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት በመፈፀም ወይም የጨረታውን ሂደት ለማዛባት መሞከራቸው ከተረጋገጠ ከጨረታው ይታገዳሉ፣ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ሳይመለስላቸው ለመንግስት ገቢ ይደረጋል በተጨማሪም በዓመቱ በሚካሄዱ ጨረታዎችም እንዳይሳተፉይ ደረጋል።

17. የጨረታ ውጤት በከተማ ከንቲባ ኮሚቴው ከፀደቀ በኋላ ጨረታው በተከፈተ ሰባት የስራ ቀናት ውስጥ በማዘጋጃ ቤቱ የመሬት ሊዝ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደቡብ ንጋት ጋዜጣይ ወጣል።

18. ተጨማሪ ዝርዝር ካስፈለገ በጨረታ ሰነዱ ላይማግኘት ይቻላል።

ለተጨማሪ መረጃ በስል ክቁጥር 046-556-00-08 / 0912 122 401 / ደውለው መጠየቅ ይችላሉ!

በድህረገፅ www.halabamun.gov.et

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *