የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Apr 29, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

.

የተበዳሪ ስም

የንብረቱ አስያዥ ስም

የይዞታው አይነት/ የሚሰጠው አገግሎት

አድራሻ

 

የይዞታው ስፋት (.)

የባለቤትነት መታወቂያ ቁጥሩ

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)

ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት

1

አቢሲኒያ የቄራ አገልግሎት .የተ.የግ.

ምንተስኖት የእንጨት እና የብረታ ብረት ስራ .የተ.የግ.ማህበር

ቅይጥ ተግባር ያለዉ መጋዘን

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ቀበሌ 03

2200

302/2007

40,723,428.03

21/09/2018 . 300-400 ጠዋት

2

አቢሲኒያ የቄራ አገልግሎት .የተ.የግ.

ኪሩቤል ተሾመ

 

ለኢንደስትሪ አገልግሎት የሚዉል መጋዘን

በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ሰበታ ከተማ ቀበሌ 04

3000

L/2868/2002

23,351,132.11

21/09/2018 . 400-500 ጠዋት

3

ሸኮ አሞራ ገደል የቡና አምራች ገበሬዎች ሁለገብ /የተ//ሥራ ማህበር

ተበዳሪው

የቡና መፈልፈያ ድርጅት

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ መሀል ሽኮ ቀበሌ

28,350

527/33/2014

4,214,686.25

21/09/2018 . 500-600 ጠዋት

በመሆኑም፡

1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።

2. ጨረታዉ የሚከናወነዉ አምባሳደር አካባቢ በሚገኘዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በሚገኘዉ አዳራሽ ቁጥር 4203 ነው።

3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።

4. ለጨረታ ከቀረቡ የመኖሪያ ቤቶች ዉጪ የሆኑ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።

5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።

6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።

7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ 15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስ.. 011-113-0508 ወይም አምባሳደር አካባቢ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና /ቤት 42 ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *