Addis Zemen (May 07, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018ዓ/ም በጀት በወረዳዉ ዉስጥ ለሚገኘዉ ባህልና ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት ባለቤትነት ለማሠራት ያሰበዉን የኦጀምታ ፍል ዉኃን ለማልማት የእንግዳ መቀበያ እና ማረፍያ፤ የወንድ እና የሴቶች ማደሪያ የመረጃ ዴክስ፤ የዘበኛ ቤት እና ሽንት ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡–
1ኛ ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
2ኛ ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስችል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፣
3ኛ ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የብቃት ማረጋገጫ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡–
4ኛ/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/ ማቅረብ የሚችሉ፡–
5ኛ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 ቀናት አየር ላይ ይዉላል።
6ኛ/ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃዳችሁን ቴክኒካል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማያያዝ በጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀዉን የመጫረቻ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ/በመክፈል እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
7ኛ/ ደረጃ 9/ዘጠኝ እና ከዝያ በላይ
8ኛ/መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9ኛ/ጨረታው ሕጋዊ ወኪሎች ድርጅቶች በተገኙበት በ22ኛው ቀን 8:00 ታሽጎ በዛው ቀን 8:30 የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡–
ተጫራቾች በጨረታዉ ያሸነፉትን ግንባታ በተባለው ጊዜ ዉስጥ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ጨርሰው ማስረከብ አባቸው።
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ ፡–የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 09 17 77 16 04 እና 09 10 15 11 28 ላይ መደወል ይችላሉ
የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት