Addis Zemen (May 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥነ–ምግባርና ፀረ–ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል እና ባይስክል/Bicycle/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
በዚህ መሠረት፡–
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የ2018 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን የተወጡ፣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ለሥራው በቂ ልምድና አቅም ያላቸዉ።
2. ተጫራቾች ለግዥ የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሲዳማ ብ/ክ/መ/ሥነ– ምግባርና ፀረ–ሙስና ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር 20 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሠነድ ጋር በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የስነ–ምግባርና ፀረ– ሙስና ኮሚሽን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት ይችላሉ።
5. የጨረታ ሣጥኑ የሚታሸገው በ16ኛው የሥራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በእለቱ በ5፡00 ሰዓት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሥርዓቱን አያስተጓጉልም።
6. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ፡– የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮሚሽን ስልክ ቁጥር 046 212 7634 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥነ–ምግባርና ፀረ–ሙስና ኮሚሽን