Addis Zemen (May 09, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር— ECC 001/2018
ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ነክ ዕቃዎች ቋሚ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን ሽያጭ
1. የኢፌደሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ነክ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
2. ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/7 አዋጅ መሠረት ይሆናል። ዕቃዎች፣ ቋሚ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን ሽያጭ የሚከናወነው ማናቸውም ኢትዮጲያዊ ዜግነት ያለው ወይም በኢትዮጲያ ህግ መሠረት የተቋቋመ የንግድ ድርጅት ያለው ሊሳተፍ የሚችል ሲሆን ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ንብረቶችን መመልከት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ መነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. የጨረታው ሰነዱ የሚገባበት አድራሻ የኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን ንብረት አስተዳደር ዳይክቶሬት ኛ ፎቅ ነው፡፡
8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ 12ኛ ፎቅ ይከፈታል፡ ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ የጨረታ መክፈቻ ሥነ–ሥርዓቱ ላይ ባይገኝ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፉበትን ዕቃዎች የቅሬታ ማቅረቢያው ጊዜ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ካለፈ በኃላ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ገንዘብ ከፍለው በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
10. አሸናፊ ተጫራች ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ይሰረዛል፡፡
11. መ/ቤቱ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡– መሿለኪያ በሚገኘው ጥላሁን ገሠሠ አደባባይ ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት
አጠገብ የሚገኘው ይርጋ ኃይሌ ህንፃ የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዳይክቶሬት
ስልክ ቁጥር 0116733725
የኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን