Addis Zemen (May 09, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጉምሩክ ኮሚሽን የአ.አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 82/2018፣ 83/2018፣ 84/2018፣ 85/2018፣ 86/2018፣ 87/2018፣ 88/2018፣ እና 89/2018 የጨረታ ማስታወቂያ፤ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ–ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፡ ጫማዎች፣ ጊርቦክስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 82/2018 በ03/09/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 83/2018 በ 6/09/2018 ዓ.ም፣ጨረታ ቁጥር 84/2018 በቀን 10/09/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 85/2018 በቀን 13/09/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 86/2018 በቀን 17/9/2018 ዓም፤ ጨረታ ቁጥር 87/2018 በ21/09/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 88/2018 በቀን 24/9/2018 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 89/2018 በቀን 27/09/2018 ዓ.ም በመሆኑ የቀጣይ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲወጣልን እየጠየቅን ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን፡፡
በመሆኑም
1. በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፡የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጥዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩከ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ ግንቦት 03/2018 ዓ/ም፣ ግንቦት 6/2018 ዓ.ም፣ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም፣ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም፣ ግንቦት 17/2018 ዓ/ም፣ ግንቦት 20/2017 ዓ/ም፣ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም፣ ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፤ የተጫራቾች ስም አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6 ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው፡፡
9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
10. በተራ ቁጥር 01 – 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሃራጅ ጨረታ ቁጥር ቁጥር 82/2018 በቀን 03/9/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 83/2018 በቀን 06/09/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 84/2018 በቀን 10/9/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 85/2018 በቀን 13/9/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 86/2018 በቀን 17/9/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 87/2018 በቀን 20/9/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 88/2018 በቀን 24/9/2018 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 89/2018 በቀን 27/9/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፤ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
11. በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00/መቶ ሺህ/ ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION .
12. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳዉቃልን፡፡
13. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃልን፡፡
14. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 684 537 እና 0116 684 193 ደውሎ ይጠይቁ፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን የአ.አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት