በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 50 ሲሲ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 50 ሲሲ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 10, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 06/2018

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ለሚገኙ ሴከተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 50 ሲሲ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ትችላላችሁ:

  1. ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ወይም አዲስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
  4. የአቅራቢነት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. የግዢው መጠን ከብር 500,000/ አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ አይነት፣ የአምራቹን ስምና የተመረተበት . በዝርዝር ከዋናው ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  8.  ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ሲጠየቁ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንከ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ 9 ቀናት የሚቆይ/ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ከኦርጂናል ዶክመንት ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  10. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 100/አንድ መቶ ብር ብቻ/ ለጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመከፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
  11. ተጫራቾች አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ዶክመንት በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በሰም በማሸግ እስከ 16ኛው ቀን 600 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት የጨረታ ሰነድ ያለበትን ሳጥን ታሽጐ በዚሁ እለት ከቀኑ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡
  13. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በውሉ መሠረት ዕቃዎቹን ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  14. /ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡

ለበለጠ መረጃ /ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113300112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣

  • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
  • በጨረታው ሂደት ውስጥ ተሻሽሎ የወጣው አዲሱ የክልሉ የግዢ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *