ቡና ባንክ አ.ማ. ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ቡና ባንክ አ.ማ. ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (May 10, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር ቡባ/ሕአዳ/ሐራጅ/033/

ቡና ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁ 97/1990 (እንደተሻሻለው) እና በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪ ስም

የንብረት አስያዥ ስም

አበዳሪ ቅርንጫፍ

ለጨረታ የቀረበው ንብረትና የቦታ ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር

 

ጨረታው የሚከናወንበት

ጨረታው የወጣው

 

 

ለጨረታ የቀረበው ንብረት

ከተማ/ክ/ከተማ ቀበሌ ወረዳ የቤት ቁጥር

 

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት

 

 

ቀን

 

ሰዓት

 

 

1

አቶ ታምሩ አብዲሳ ገሰሰ

ተበዳሪ

 

ዓብይ

 

የመኖሪያ ቤት

 

በአዲስ አበባ ከተማ፤ ቂሪቆስ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 5፣ እልልታ ሪል እስቴት 8ኛ ወለል ላይ የሚገኝ

አፓርታማ

AA0000040500 0012010802

 

272.85

36,958,148.55

ሰኔ 2 2018 ዓ.ም

 

4፡00-5፡00

ለሦስተኛ ጊዜ

 

 

2

አቶ መሳይ ገረመው (መሳይ ገረመው ህንጻ ሥራ ተቋራጭ)

ወ/ሮ ትዕግስት ጋሻው እርቅይሁን እና አቶ በሱፈቃድ ታደለ ሲሳይ

ሻላ

መናፈሻ

 

ቅይጥ የመኖሪያ አገልግሎት G+5

 

በአዲስ አበባ ከተማ፤ ልደታ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08 ወጣት ማዕከል አካባቢ

AA0000309

00043/B

 

250 ካ.ሜ

 

55,045,136.85

 

ሰኔ 2 2018 ዓ.ም

5፡00-6፡00

ለመጀመሪያ ጊዜ

 

ተሽከርካሪ

ተ.ቁ

የተበዳሪ ስም

የንብረት አስያዥ ስም

አበዳሪ ቅርንጫፍ

 

የሰሌዳ ቁጥር

የመያዣ አይነት/ ሞዴል

የሻንሲ ቁጥር/

ሴሪያል ቁጥር

የሞተር ቀጥር

 

የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር

የጨረታ ቀን እና ሰዓት

 

ጨረታው

የወጣው

 

አቶ ሮቤል አለማየሁ አሰፋ

አቶ በረከት አለማየሁ አሰፋ

ዓብይ

 

አአ-02-B79009

የ2020 ስሪትታይላንድ ሚትስቡሺ አውቶሞቢል

MMDAFT6J8 MH004326

3A92KB9852

 

1,900,000.00

ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም

4:00-5:00

 

ለመጀመሪያ

ጊዜ

 

                       

የሐራጅ ደንቦች

1.ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በቡና ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::

2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ መክፈል አለበት:: ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ:: ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል::

3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፤ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው:: ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::

4. የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም::

5. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር በዋጋው ላይ የሚታሰብ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው አሸናፊው ይከፍላል::

6. በሐራጁ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ለማየት ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር በመነጋገር ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል::

7. ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው:: 

8. ጨረታው በቡና ባንክ ኢማ ዋናው መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ፤ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ወደ ቦሌ ሲሄዱ ሩዋንዳ መታጠፊያ ሳይደርሱ በሚገኘው የባንኩ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ የሚካሄድ ይሆናል::

9 በተራ ቁጥር 1 ለተገለጸው የመኖሪያ ቤት የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መስፈርት ለሚያሟሉ ተጫራቾች ባንኩ እስከ 70% ብድር ያመቻቻል::

10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስ.ቁ 011-1-58-08-63/011-1-26-36-09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *