Reporter (May 10, 2026)
የኦዲት ሥራ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ የየ2015/16 እና የ2016/17 ዓ ም የሂሳብ ኦዲት ሥራን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል::
1.የኮሌጁ ዓላማ፡– በኮሌጁ ሒሳብ ክፍል የሚገኘውን የሒሳብ ሠነዶችና በኮሌጁ የሂሳብ ክፍል የተሠራውን ወርሃዊና ዓመታዊ የሂሳብ አያያዝና ሪፖርቶችን መርምሮ ለኮሌጁ ማኔጅመንት ማቅረብ ነው:: ቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ በ2015/16 እና የ2016/17 ዓ.ም በጀት ዓመት በድርጅቱ የሂሳብ ክፍል የተዘጋጁትን የሂሳብ መግለጫዎችን በዓለም አቀፍ የኦዲት ደረጃዎች መሠረት የኮሌጁን የፋይናንስ እንቅስቃሴና ንብረት አስተዳዳር እና የኮሌጁን ገቢና ወጪ እንዲሁም ተሰብሳቢ ሂሳብ ተቀባይነት ባለው የሂሳብ አሰራር መርህ መሠረት የተሠራ መሆኑን በዝርዝር አጣርቶ ሚዛናዊ አስተያየት ወይንም ሪፖርት ማቅረብ ነው::
2. በምርመራ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ዝርዝር፡–
ኮሌጁ ይህ የሂሳብ ምርመራው እንዲከናወንለት የሚፈልገው ዝርዝር የአሠራሩ ተግባራት የተጠቀሱበት በዓለም አቀፍ የኦዲቲንግ ህግና አሠራር /international Auditing and Reporting Procedure/ መሠረት ሆኖ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ነው::
1.0.ጨረታውን ለመወዳደር የቀረቡ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡–
1.1. የመርማሪ ኦዲት ድርጅቱ ከምንም እና ከማንም ተፅዕኖ ነፃ የሆነና ይህን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡-
1.2. ኦዲት ለማድረግ የተሰጠው ሕጋዊ የታደሰ የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፡–
1.3. ከዚህ በፊት ለ5 ተከታታይ ዓመታት የኦዲት ሥራን የሠራና ለዚህም የማስረጃ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፡–
1.4. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፋቃድ ፣የግብር ከፋይነት ሠርተፊኬት፣እንዲሁም ላለፉት 3 ዓመታት ተገቢውን ግብር የከፈለበትን ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፡–
1.5. የኦዲት ሥራው የሚጠናቀቅበትን የጊዜ ገደብ ማለትም ረቂቁንና የመጨረሻውን የማስረከቢያ ጊዜን በዕቅድ ማቅረብ የሚችል፤
1.6. ተጫራቾች ከላይ በዝርዝር በተገለጸው መስፈርት መሠረት ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርትር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ልደታ በሚገኘው ቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ዋና ማስገባት የሚችል ሲሆን
1.7. በዚህ የጨረታ ውድድር ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ እና ቢዚነስ ኮሌጅ
አድራሻ፡– አ.አ. ቅድስት ልደታ ቤተ ክርስትያን ጎን
ለበለጠ መረጃ ስ ቁ. 0922 584460/0911 412830/0911 667066