ዳሸን ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ እና ከኣዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ ከ900 በላይ ለሚሆነ የባንኩ የቀጠና ፅ/ቤቶች እና ቅርንጫፍ ባንኮች የጽዳት፣ የመልዕክተኛ እና ሻይና ቡና ጥቅል አገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዳሸን ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ እና ከኣዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ ከ900 በላይ ለሚሆነ የባንኩ የቀጠና ፅ/ቤቶች እና ቅርንጫፍ ባንኮች የጽዳት፣ የመልዕክተኛ እና ሻይና ቡና ጥቅል አገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


Reporter (May 10, 2026)

ግልፅ ጨረታ የማስታወቂያ ጥሪ

የጨረታ ቁጥር DBOT15725/20

ዳሸን ባንክ አማ በአዲስ አበባ እና ከኣዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ 900 በላይ ለሚሆነ የባንኩ የቀጠና /ቤቶች እና ቅርንጫፍ ባንኮች የጽዳት፣ የመልዕክተኛ እና ሻይና ቡና ጥቅል አገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

1. መግቢያ

ይህ የጨረታ ሰነድ በዳሽን ባንክ አክሲዮን ማህበር የጽዳት፤ የመልዕክተኛ እና ሻይና ቡና ጥቅል የሥራ አገልግሎት አቅራቢዎችን ጥሪ ለማድረግ የተዘጋጀ ሰነድ ነው:: የዚህ ጨረታ ዓላማም በዘርፉ በቂ የሥራ ልምድና አደረጃጀት ያላቸውን ህጋዊ ድርጅቶች በመምረጥ ባንኩ በሚሰጠው የሥራ ጥራት ደረጃ (Serve level Standard) መሰረት በተገቢው መንገድ የፅዳት የመልዕክት እና የሻይ ቡና ሥራ ለማሰራት ማስቻል ነው::

2. የፅዳት መልዕክት እና ሻይና ቡና ማስተንግዶ አገለግሎት ግዥ ዓላማ፤

ሙያዊ ብቃት ባለቸው ሰራተኞች እና ደረጃቸውን የጠበቁ የፅዳት ዕቃዎችን በመጠቀም የባንኩን ቢሮ እና አካባቢ ፅዱ እና ውብ ለስራ አመቺ ሁኔታ በመፍጠር እንዲሁም የመልዕከት እና ሻይና ቡና አገልገሎት በማቅረብ የባንኩን ስራተኞችና ደንበኞች በማርካት የባንኩ ሰራተኞች በዋና ስራቸው ላይ ትኩረት በማድረግ በስራቸው አመርቂና ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ነው::

3. የአገልግሎቱ ይዘት፣

3.1 አገልግሎት ሰጪ የባንኩን ቢሮዎች፤ ቅርንጫፎች፣ መጋዘኖች ወይም ባንኩ የሚጠቀምባቸው ሌሎች ቦታዎች ከባንኩ በተሰጠው የሥራ መስፈርት የሰው ኃይል እና ማቴሪያል በማቅረብ አገልግሎት መስጠት፣

3.2 ባንኩ እንደ አስፈላጊነቱ ለተለያዩ አገልግሎት አቅራቢዎች በቀጠና ወይም በቅርንጫፍ በማከፋፈል ውል ሊሰጥ ይችላል፣

3.3 ባንኩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

4. ተፈላጊ የሰነድ ማስረጃዎች፣

4.1 ድርጅቱ በዘርፉ በቂ ልምድ ያለውና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

4.2 የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የወቅቱን ግብር የከፈሉ፣

4.3 ከባንኮች ጋር ወይም ትላልቅ ድርጅቶች ጋር በመስራት ልምድ ያለው!

4.4 ከዚህ በፊት ከሰራበት ድርጅት የመልካም የስራ አፈፃጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

4.5 ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከልሎች ለመስራት አቅምና ፍላጎት ያለው

4.6 የባንኩ ቅርንጫፎች ባሉበት ከተሞች ቢሮ እና ተወካይ ሰራተኛ ያለው

4.7 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር) የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፣

5. ተፈላጊ የሰውና የማቴርያል ግብአቶች፣

5.1 ደረጃቸውን የጠበቁ የፅዳት ማቴሪያሎችን በማቅረብ እና በመጠቀም ባንኩ በሚሰጠው የሥራ ጥራት ደረጃ (Service level Standard) መሰረት በተገቢው መንገድ የፅዳት የመልዕክተኛ እና የሻይ ቡና አገልግሎት ሥራ መስራት የሚችል ብቁ ሰራተኞችን የሚያቀርብ፣

5.2 ለቁጥጥር እና አስፈላጊ ግብአቶችን ለማቅረብ የሚውሉ መኪናዎች ያሉት፣

5.3 በባንኩ የሰው ኃብት ምደባ እቅድ መሰረት አስፈላጊውን የሰው ኃይል ለማሰማራት የሚችል፣

5.4 ብቁ ሰራተኞችን በማሰልጠንም ይሁን ለስራው ቅጥር መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰራተኞችን በመመደብ ማሰማራት የሚችል::

6. አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜ፣

ባንኩ አገልግሎቱን ለአንድ ዓመት የሚያሰራ ሲሆን እንደ ድርጅቱ የስራ አፈፃፀም ምዘና እና እንደ ባንኩ ውሳኔ የአገልግሎት ጊዜውን ለሁለት ዓመታት ሊያራዝም ይችላል::

7. የጨረታ መሸጫ፣ማስገቢያና መክፈቻ ቀን፣

7.1. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ድረገጽ https://bids.extratenders.com/bids-shop/dashen-bank-sc/ ወይም https://dashen.afrotender.com/orafrotender.com; ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከግንቦት 03 እስከ ግንቦት 17 ቀን 2018 / ድረስ ይሆናል::የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሥራ ቀናት ከጧት 200 እስከ 600 ከሰዓት ደግሞ 700 እስከ 1100 ከታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመምጣት ወይም ከላይ በተገለጸው ድረገጽ ላይ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ የማይመልስ በመከፈል መግዛት ማውረድ ይችላሉ::

7.2. በአካል ሰነድ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በዳሸን ባንክ አካውንት 180020002 በየትኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ አስገብተው ስሊፕ (slip) ወይም ማረጋገጫ የጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ማቅርብ ይኖርባቸዋል::

7.3. ጨረታው የሚዘጋው ግንቦት 17 ቀን 2018 / ከቀኑ 1100 ሰዓት ሲሆን መክፈቻ ቀን በጊዜያዊነት ደግሞ ግንቦት 18 ቀን 2018 / ከቀኑ 800 ከታች በተገለፀው አድራሻ ይሆናል::

7.4. ባንኩ የተሻለ ነገር ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ዳሸን ባንክ ዋናው /ቤት

ብሔራዊ ባንክ ፊት ለፊት  

ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት መምሪያ

ቢሮ ቁጥር 7 ወለል

ስልክ 0115 180 356 የውስጥ ቁጥር 4171/3153

ዳሸን ባንክ ሁልጊዜ አንድ እርምጃ ቀዳሚ!


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *